Skip to main content

የቋንቋ አገልግሎት - አማርኛ (Amharic)

የተተረጎሙ ምንጮች

የኢንተርኔት አሳሽ ትርጉም (መደቡን መምረጥ)

የሚችጋን ስቴት መምሪያ (Michigan Department of State) በሦስተኛ አካል መተግበሪያ ወይም ኢንተርኔት አሳሽ በኩል የተሠራውን ማንኛውንም ትርጎሞችን በመጠቀም ለሚከሰተው ማንኛውም ወይም ሙሉ በሙሉ ክስረት ኃላፊነት እና ቅሬታን የማይቀበል መሆኑን ይገልጻል። የሦስተኛ አካል አገልግሎትን መጠቀም በተጠቃሚው በራሱ ኃላፊነት ይሆናል። ከሦስተኛ አካል አገልግሎቶች ጋር በተያያዘ ያለው መረጃ እንደ አመቺነቱ ብቻ የሚሰጥ ይሆናል።

ዴስክቶፕ
ትርጉሞችን በአረብኛ፣ ቻይንኛ (የተቃለለ)፣ ፈረንሳይኛ፣ ጀርመንኛ፣ ጣልያንኛ፣ ጃፓንኛ፣
ኮርያኛ፣ ፖርቹጋልኛ፣ ሩስያኛ፣ እና እስፔንኛ ማግኘት ይችላሉ።

  1. የ ሳፋሪ (Safari) አሳሽን ይክፈቱ እና View ን ይምረጡ፣ ከዚያም ከተቆልቋይ ምናሌው Translation ን ይምረጡ። የእርስዎን አሳሽ በሚመርጡት እና ከእንግሊዝኛ ውጪ የሆነ ቋንቋ ይሙሉ።
  2. መተርጎም ወደሚፈልጉት ድረገጽ ይሂዱ።
  3. የተርጉም (Translate) ቁልፍ ከአድራሻ አሞሌ በስተቀኝ በኩል ይታያል። ለሁሉም ገጾች ትርጉሞች ላይገኙ ይችላሉ።
  4. የተርጉም ቁልፍን እና የእርስዎን ተመራጭ ቋንቋ ይምረጡ።

አይፎን (iPhone) ወይም አይፓድ (iPad)

ሳፋሪ (Safari) በስልክ ላይ
ትርጉሞችን በአረብኛ፣ ቻይንኛ (የተቃለለ)፣ ፈረንሳይኛ፣ ጀርመንኛ፣ ጣልያንኛ፣ ጃፓንኛ፣
ኮርያኛ፣ ፖርቹጋልኛ፣ ሩስያኛ፣ እና እስፔንኛ ማግኘት ይችላሉ።

  1.  በተንቀሳቃሽ መሳሪያዎ ላይ የሳፋሪ (Safari) አሳሽን ይክፈቱ እና ለመተርጎም ወደሚፈልጉት ድረገጽ ይሂዱ።
  2. የጣቢያ አማራጮችን ለመመልከት ከአድራሻ አሞሌ ጎን ያለውን የ aA አዶ ይምረጡ። ከተቆልቋይ ምናሌ ላይ፣ “Translate to” ን እና የእርስዎን ተመራጭ ቋንቋ ይምረጡ ።
  3. ብቅ ባይ ምናሌ የሚታይ ከሆነ “Enable Translation” ይምረጡ። ትርጉምን እንዲሠራ ለማድረግ አንዴ ብቻ የሚጠየቁ እንደሆነ ያስታውሱ።

ከ IOS 14.0 የቀደመ የክወና ስርዓቶች ያላቸው የአፕል (Apple) መሳሪያዎች ይህንን መለያ ባህሪ

አያካትቱም። ትርጉሞችን ለማግኘት የጉግል ትርጉም (Google Translate) መተግበሪያን ወይም ማይክሮሶፍት ተርጓሚ (Microsoft Translator) መተግበሪያን ወደ የእርስዎ መሳሪያ ያውርዱ።Safari offers browser translation in Arabic, Chinese (Simplified), French, German, Italian, Japanese, Korean, Portuguese, Russian, and Spanish.

ዴስክቶፕ

  1. የ ክሮም (Chrome) አሳሽን ይክፈቱ እና ለመተርጎም ወደሚፈልጉት ድረገጽ ይሂዱ።
  2. ብቅ ባይ የጉግል ትርጉም (Google Translation) ምናሌ ከአድራሻ ምናሌው በታች ሊታይ ይችላል። ገጹን ለመተርጎም ከምናሌው ላይ ምርጫዎ የሆነውን ቋንቋ ይምረጡ።
  3. የትርጉም ምናሌ የማይመጣ ከሆነ፣ ከአድራሻ ምናሌ በስተቀኝ በኩል የጉግል ትርጉም (Google Translate) ቁፍን ይምረጡ። ገጹን ለመተርጎም ከምናሌው ላይ ምርጫዎ የሆነውን ቋንቋ ይምረጡ። 
  4. ለትርጉም ተጨማሪ ቋንቋዎችን ለማግኘት፣ ከአድራሻ ምናሌ በስተቀኝ በኩል የጉግል ትርጉም (Google Translate) ን ቁልፍ ይምረጡ፣ ከዚያም በኋላ የእርምጃ ምናሌ አዶን ይምረጡ። ከተቆልቋይ ምናሌ ውስጥ፣ “Choose Another Languages” የሚለውን ይምረጡ እና ከተቆልቋይ ምናሌ እርስዎ ምርጫ የሆነውን ቋንቋ ይምረጡ።

አንድሮይድ (Android) ስልክ ወይም ታብሌት

  1. በተንቀሳቃሽ መሳሪያዎ ላይ የክሮም (Chrome) አሳሽን ይክፈቱ እና ለመተርጎም ወደሚፈልጉት ድረገጽ ይሂዱ።
  2. የጉግል (Google) ትርጉም ምናሌ በማያ ገጹ ግርጌ ላይ ሊታይ ይችላል። ገጹን ለመተርጎም ከምናሌው ላይ ምርጫዎ የሆነውን ቋንቋ ይምረጡ።
  3. ለትርጉም ተጨማሪ ቋንቋዎችን ለማግኘት፣ የእርምጃ ምናሌ አዶን ይምረጡ እና “More Languages” የሚለውን ይምረጡ፣ ከዚያም ከተቆልቋይ ምናሌው ውስጥ የእርስዎ ምርጫ የሆነውን ቋንቋ ይምረጡ።
  1. የማይክሮሶፍት ኤጅ (Microsoft Edge) አሳሽን ሲከፍቱ፣ በአስሽዎ የቀኝ ጥግ ማዕዘን ላይ የሚገኙትን ሦስት ነጥቦች ጠቅ ያድርጉ፣ ከዚያም ከተቆልቋይ ዝርዝሩ “Settings” የሚለውን ይምረጡ።
  2. ከአሳሽዎ መስኮት በስተግራ በኩል፣ “Languages” የሚለውን ይምረጡ ከዚያም “Add languages” የሚለውን በመምረጥ እና መጠይቆቹን በመከተል የእርስዎ ምርጫ የሆነውን ቋንቋ ያዘጋጁ።
  3. በእርስዎ ምርጫ በሆነው ቋንቋ ያልተተረጎመ ገጽ ከጎበኙ፣ በአድራሻ አሞሌው ላይ ብቅ ባይ የትርጉም ምናሌ ሊታይ ይችላል። የእርስዎ መርጫ የሆነውን ቋንቋ ለመምረጥ መጠይቆቹን ይከተሉ እና ገጹን ለመተርጎም “Translate” የሚለውን ይምረጡ።
 

የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ግብይቶች እና አገልግሎቶች

  • የተመደበው የቅርንጫፉ ትርጉም

    የሚከተለው የቅርንጫፍ ቢሮዎች በስልክ የትርጉም አገልግሎቶችን ይሰጣሉ። በቀጠሮዎ ቀን ይህን አገልግሎት ለማግኘት እንዲችሉ መጠየቅ ይኖርብዎታል። አስተርጓሚ ለማግኘት ቀደም ብሎ ማሳወቅ ወይም መጠየቅ አያስፈልግም። ለእገዛ ወይም ለድጋፍ፣ እባክዎን በ MDOS-Access@Michigan.gov. ኢሜይል ያድርጉ።

    የትርጉም አገልግሎቶችን መፈተሽ

    ፈተና መውሰድ ከፈለጉ፣ ፍቃድን ድጋሚ ሚያገኙበት የፍርድ ቤት ሂደት ካለብዎት፣ ወይም የፍቃድ ፈተና በድጋሚ መውሰድ ከፈለጉ፣ ከተያዘው ቀጠሮዎ በፊት አስቀደመው በሚቺጋን የውጭ ጉዳይ አማካሪ (Michigan Department of State) ፍቃድ የተሰጠውን አስተርጓሚ መጠቀም አለብዎት።

    ለሁሉም ሌሎች የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር አገልግሎቶች እና ለቢሮ ቀጠሮዎች፣ እርስዎን ወክሎ እንዲያስተረጉም ማንኛውንም ሰው መጠየቅ ይችላሉ።

    ቋሚ በጎ ፍቃደኛ አስተርጓሚዎች

    የሚቺጋኑ የውጭ ጉዳይ አማካሪ (Michigan Department of State) ቋሚ የውጪ ቋንቋ አስተርጓሚዎችን ዝርዝር ይይዛል። ወደ የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ቢሮ ቦታ የሚያደርጉትን ጉብኝት ለማመቻቸት፣ በጎ ፍቃደኛ አስተርጓሚን ማነጋገር ይችላሉ።

    በዚህ ዝርዝር ውስጥ ያሉ አስተርጓሚዎች በማንኛውም የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ቢሮዎች የትርጉም አገልግሎት እንዲሰጡ ፍቃድ ያላቸው ሲሆን የአገልግሎቱን ክፍያ እንዳይጠይቁ ይከለከላሉ።

    ቀድሞ የጸደቀውን የአስተርጓሚዎች ዝርዝር ቅጂ ለመጠየቅ፣ የውጭ ጉዳይ ፀሐፊ ቢሮን ይጎብኙ ወይም ወደ MDOS-Access@Michigan.gov ኢሜል ያድርጉ።

    የአንድ ጊዜ በጎ ፍቃደኞች

    ለፈተና፣ ለፍርድ ቤት ችሎት ወይም ለድጋሚ ፈተና እርስዎን ወክሎ የሆነ ግለሰብ እንዲያስተርጉም ከፈለጉ፣ እንደ የአንድ ጊዜ አስተርጓሚ ሆነው ለማገልገል ማመልከቻ ማስገባት ይኖርባቸዋል። የአንድ ጊዜ አስተርጓሚዎ ዕቅድ ከተያዘለት ጉብኝትዎ በፊት በውጭ ጉዳይ አማካሪው ፈቃድ ሊሰጠው ይገባል እንዲሁም ለፈተናዎ፣ ለፍርድ ቤት ችሎትዎ ወይም ለድጋሚ ፈተናዎ ብቻ መተርጎም ይችላል።

    የአንድ ጊዜ አስተርጓሚ ለመሆን ማመልከቻ ለማስገባት፣ አንድ ግለሰብ የሚከተሉትን ማድረግ አለበት፡-

    • እንደ የአንድ ጊዜ አስተርጓሚ እንደሚያገለግሉ የሚገልጸውን በመምረጥ የበጎ ፈቃደኛ የትርጉም አገልግሎት ለመስጠት ማመልከቻ መሙላት እና መፈረም።
    • ትክክለኛ፣ ጊዜው ያላለፈበት የመንጃ ፍቃድ ወይም መታወቂያ ፎቶ ወይም ቅጂ ማቅረብ አለባቸው

    የሚያስፈልጉትን ሰነዶች በፖስታ፣ በፋክስ ወይም በኢሜል ወደ፦ 

    Michigan Department of State
    Enforcement Division
    P.O.Box 30708
    Lansing, MI 48909 ይላኩ
    ፋክስ፦ 517-335-3241
     ኢመል፦ SOS-OIS@Michigan.gov

    መምሪያው አንድ ጊዜ ማመልከቻውን ከተመለከተ በኋላ፣ አመልካቹ የአንድ ጊዜ የአስተርጓሚ አገልግሎት እንዲሰጥ ፍቃድ ሲያገኝ ሠራተኞች አመልካችን ያሳውቃሉ።

    የበጎ ፍቃደኛ የአስተርጓሚ አገልግሎቶችን ለማቅረብ የሚቀርብ ማመልከቻ.

    Application to Provide Volunteer Interpreter Services

  • ሁሉም የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቢሮዎች ለአሽከርካሪ እውቀት መመዘኛ ፈተናዎች የተተረጎሙ ፈተናዎችን በሚከተሉት ቋንቋዎች ያቀርባሉ፦

    • እንግሊዘኛ
    • አልባኒያኛ
    • አረብኛ
    • ቻይንኛ
    • ፈረንሳይኛ
    • ግሪክኛ
    • ሂንዲ
    • ጣልያንኛጃፓንኛ
    • ኮርያኛ
    • ፖላንድኛ
    • ፖርቹጋልኛ
    • ሩስያኛ
    • ስፐይንኛ
    • ዩክሬንኛ
    • ቬትናምኛ

    የአሽከርካሪው፣ ትንሹ ሞተር ሳይክል፣ ሞተር ሳይክል፣ እና የመዝናኛ (ደብል R) የእውቅና ፈተናዎች በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቢሮዎች ውስጥ በሚከተለው ቋንቋዎች ይሰጣሉ፦

    • እንግሊዘኛ
    • ስፐይንኛ
    • አረብኛ

    Schedule an office visit

    New drivers

    License and ID information

  • የተሽከርካሪ ታርጋ እድሳት፣ የመንጃ ፍቃድ ወይም የስቴት መታወቂያ (ID) እድሳት እና የባለቤትነት ጥያቄ ማቅረብን ጨምሮ ብዙ ግብይቶች በኦንላይን ሊጠናቀቁ ይችላሉ። በአሳሽዎ (browser) ላይ በራስ-የሚተረጉም ባህሪን በመጠቀም ድህረ-ገጻችንን ማግኘት እና በመረጡት ቋንቋ ኦንላይን ክንውኖችን ማጠናቀቅ ይችላሉ። የዉጭ ጉዳይ አማካሪን ድህረ-ገጽ በራስ-የመተርጎም መመሪያዎችን ለማየት የቀደመውን ገጽ ይጎብኙ።
    Go to Online Services

  • የአሽከርካሪ ምዝገባዎን፣ ሰነድ፣ እና ታርጋ ለማሳደስ ወይም የመንጃ ፍቃድዎን ወይም መታወቂያዎን ለማሳደስ አዲስ ፎቶ የማያስፈልግ ከሆነ ራስ-አገልግል ጣቢያዎችን ይጎብኙ። ሁሉም 160 የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ራስ-አገልግል ጣቢያዎች በሚከተሉት ቋንቋዎች የተተረጎሙ አገልግሎቶችን ያቀርባሉ።

    • አረብኛ
    • ቤንጋሊ
    • እንግሊዘኛ
    • ፈረንሳይኛ
    • ማንደሪን
    • ፓሽቶ
    • ስፐይንኛ
    • ቬትናምኛ

    በራስ-አገልግል ጣቢያ ላይ ለሚደረግ ለእያንዳንዱ ዕቃ ግብይት የ$3.95 የአገልግሎት ክፍያ ይከፈላል።

    Find a self-service station

  • አብዛኛዎቹ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ግብይቶች በኦንላይን ወይም በፖስታ ሊጠናቀቁ ይችላሉ። ብዙ የመንጃ ፍቃድ እና የመታወቂያ ግብይቶች እና አብዛኛዎቹ የተሽከርካሪዎች ታርጋ እድሳት ግብይቶች በራስ-አገልግል ጣቢያ ሊደረጉ ይችላሉ። የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርን ቢሮ መሄድ የሚያስፈልግዎት ከሆነ፣ የቢሮ ጉብኝት ቀጠሮ እንዲያስይዙ በጥብቅ ይበረታታል። ጉብኝቶች እስከ ስድስት ወራት ለሚደርስ ጊዜ ቀድመው ሊያዙ ወይም ለቀጣዩ ቀን ቀጠሮ ሊያዝላቸዉ ይችላል። በሺዎች የሚቆጠሩ የቢሮ ጉብኝቶች በእያንዳንዱ የሥራ ቀን (ሰኞ-አርብ) በ 8 a.m. (ከጠዋቱ) ላይ እና በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከሰዓት በኋላ ይገኛሉ። 
     
    በመረጡት ቋንቋ በኦንላይን የጉብኝት ቀጠሮ ለማስያዝ፣ በራስ-የመተርጎም ባህሪ ያለው አሳሽ እየተጠቀሙ መሆንዎን ያረጋግጡ። ወይም ወደ 888-SOS-MICH (888-767-6424) በመደወል ለቢሮ ጉብኝት ቀጠሮ ያስይዙ። 

    Schedule an office visit

    Browser translation – Language services

ምርጫዎች እና የድምጽ አሰጣጥ መረጃ

  • የሚከተሉት ከሆኑ በሚቺጋን ውስጥ ድምጽ ለመስጠት መመዝገብ ይችላሉ፡- 

    - የአሜሪካ ዜጋ 
    - ዕድሜዎ ቢያንስ 16 ከሆነ
    - በአሁኑ ጊዜ በእስር ቤት ወይም በወህኒ ቤት ውስጥ ቅጣት ላይ ካልሆኑ
    - የሚቺጋን ነዋሪ

    የምዝገባ ሁኔታዎን ይመልከቱ 

    በራስ የመተርጎም ባህሪ ያለውን አሳሽ በመጠቀም የመራጮች የምዝገባ ሁኔታዎን በ Michigan.gov/Vote ላይ ማየት ይችላሉ።

    እንዴት መመዝገብ እንደሚቻል

    ድምጽ ለመስጠት ከምርጫ ቀን እስከ 2 ሳምንታት በፊት ድረስ በኦንላይን (በሚቺጋን የአሽከርካሪ ፍቃድ እና በመታወቂያ ቁጥር) ወይም በፖስታ መመዝገብ ይችላሉ። እንዲሁም በምርጫ ቀን ከ 8 p.m. በፊት ወይም እስከዚያ ድረስ በማንኛውም ሰዓት በአካባቢዎ ፀሐፊ ቢሮ በአካል በመቅረብ መመዝገብ ይችላሉ። 

    ድምጽ ለመስጠት በፖስታ ወይም በአከባቢዎ ፀሐፊ ቢሮ ሲመዘገቡ፣ የሚቺጋን የአሽከርካሪ ፍቃድ ወይም መታወቂያ የማያስፈልግዎት ሲሆን በምትኩ የማህበረሰብ ዋስትና ቁጥርዎን የመጨረሻዎቹን አራት አሃዞች መስጠት ይችላሉ። 
    እባክዎን ያስታውሱ ምርጫ በተደረገ በ 14-ቀናት ውስጥ የነዋሪነት ማረጋገጫዎን ይዘው በአካል በፀሐፊዎ ቢሮ መመዝገብ አለብዎት።

    በኦንላይን ይመዝገቡ፦ በመረጡት ቋንቋ የኦንላይን የመራጮች ምዝገባ በMichigan.gov/Vote ላይ ለማግኘት በራስ-የመተርጎም ባህሪ ያለውን አሳሽ ይጠቀሙ።

    የሚከተለው ከሆነ በኦንላይን መመዝገብ ይችላሉ፦

    • ትክክለኛ የሚቺጋን ስቴት መታወቂያ ወይም የመንጃ ፍቃድ ካለዎት 
    • የማህበራዊ ዋስትና ቁጥርዎን የመጨረሻ 4 አሃዞች የሚያውቁት ከሆነ 
    • ዕድሜዎ ቢያንስ 16 ዓመት ከሆነ 
    • ከምርጫው ቀን ከ 14 ቀናት በፊት ከተመዘገቡ 

    ከምርጫው በ 14 ቀናት ውስጥ ወይም በምርጫ ቀን ላይ በኦንላይን ከተመዘገቡ በዚያ ምርጫ ላይ ድምጽ ለመስጠት ብቁ አይሆኑም። መታወቂያዎን ወይም የአሽከርካሪ ፍቃድዎን ወቅታዊ ካደረጉ በኋላ በ 10 ቀናት ውስጥ የኦንላይን ምዝገባ የተከለከለ ነው።

    በኦንላይን ይመዝገቡ

    Browser translation – Language services

    ሊታተም በሚችል የምዝገባ ቅጽን በመጠቀም ይመዝገቡ፦ የተተረጎመ እና ሊታተም በሚችል የመራጮች ምዝገባ ቅጽን በመጠቀም ድምጽ ለመስጠት መመዝገብ ይችላሉ። እንደሚከተለዉ ከሆነ የታተመ የምዝገባ ቅጽ በመጠቀም መመዝገብ ይችላሉ፡-

    • ትክክለኛ የሚቺጋን ስቴት መታወቂያ ወይም የአሽከርካሪ ፍቃድ ወይም የማህበራዊ ዋስትና ቁጥርዎ የመጨረሻ 4 አሃዞች (አንድ ብቻ ነው የሚፈለገው) ካለዎት።
    • ዕድሜዎ ቢያንስ 16 ዓመት ከሆነ 
    • ከምርጫው ቀን ከ 14 ቀናት በፊት ከተመዘገቡ

    ሊታተም የሚችል የድምጽ ሰጪዎች ምዝገባ ቅጽ

    በራስ-አገልግል ጣቢያ ኪዮስክ ይመዝገቡ፦ የራስ አገልግል ጣቢያዎች እንግሊዝኛ ባልሆኑ ቋንቋዎች የድምጽ ሰጪዎች ምዝገባ ግብይቶችን ያቀርባሉ። ለበለጠ መረጃ የዚህን ድህረ-ገጽ ክፍል የራስ-አገልግል ጣቢያን ይመልከቱ።

    በፀሐፊዎ ቢሮ በአካል ይመዝገቡ፦ በአካል ቀርበው ድምጽ ለመስጠት ለመመዝገብ የአከባቢዎን ፀሐፊ ቢሮ መጎብኘት ይችላሉ። ምርጫ ከመደረጉ በፊት ባሉት 14 ቀናት ውስጥ በአከባቢዎ ፀሐፊ ቢሮ በአካል ቀርበዉ መመዝገብ እና የነዋሪነት ማረጋገጫ ማቅረብ አለብዎት። የነዋሪነት ማረጋገጫ ሙሉ ስምዎን እና የአሁን አድራሻዎን የሚገልጽ ህጋዊ ሰነድ ሲሆን  የባንክ መግለጫ፣ ጊዜዉ ያላለፈበት የ MI የመንጃ ፍቃድ ወይም መታወቂያ፣ የኪራይ ውል ወይም የፍጆታ ሂሳብን ሊያካትት ይችላል።
     
    የአካባቢዎን ፀሐፊ ያግኙ

    በምርጫ ላይ ድምጽ መስጠት
    በምርጫ ላይ ድምጽ ለመስጠት የሚከተሉትን መሆን አለብዎት፡- 

    • የተመዘገበ የሚቺጋን ድምጽ ሰጪ
    • ቢያንስ 18 ዓመት የሞላዉ
    • በአሁኑ ጊዜ በእስር ቤት ወይም በወህኒ ቤት ውስጥ ቅጣት ላይ ያልሆነ 
    • ከምርጫ በፊት ቢያንስ ለ 30 ቀናት የተመሳሳዩ ሚቺጋን ከተማ፣ መንደር ወይም ሰፈር ነዋሪ የሆነ

    በሚስጥር ድምጽ የመስጠት መብት አለዎት። እንደ የሚቺጋን ከተማ ድምጽ ሰጪ፣ ምክንያት ሳያቀርቡ በማንኛውም ምርጫ ለማይገኝ ሰዉ የሚቀርብ ድምጽ መስጫ መጠየቅ እና በዛ ድምጽ መስጠት ይችላሉ። 

  • ለሚቀሩት ሰዎች የድምጽ መስጫ ወረቀትን ለማግኘት ማመልከት

    በሚቺንጋን (Michigan) እያንዳንዱ ድምጽ ለመስጠት የተዘገቡት በ ለሚቀሩት የደምጽ መስጫ ወረቀትበኩል ድምጻቸውን መስጠት ይችላሉ። የለቀሩበኢንተርኔት ቀጥታ መስመር ላይ የ AV የደምጽ መስጫ ማመልከቻ ትየድምጽ መስጫ ወረቀት ለመጠየቅ፣ ለቀሩትየድምጽ መስጫ ማመልከቻን ሞልተው ማስገባት ይኖርብዎታል። ለድምጽ መስጫ ወረቀት ማመልከቻ  


    ለመሙላት ለቀሩትያለው አማራጭ፦

    • በራስ-የመተርጎም ባህሪ ያለው አሳሽን በመጠቀም ማመልከቻውን ሞልተዉ በኦንላይን ማቅረብ። በኢንተርኔት ቀጥታ መስመር ላይ በሚከተለው ያመልክቱMichigan.gov/Vote
    • ለከተማዎ ወይም ለመንደርዎ ፀሐፊ መደወል እና የታተመ ማመልከቻ በፖስታ እንዲላክልዎ መጠየቅ። የአከባቢዎን የጽሕፈት ቤት ቢሮ በሚከተለው ያግኙ Michigan.gov/Vote
    • በፖስታ ወይም በአካል ወደ የአካባቢዎ ወይም መንደርዎ ጸሐፊ የሚመለስ ሊታተም የሚችል የተተረጎመ ማመልከቻን ማውረድ። የተተረጎሙት ቅጾች በእነዚህ ማስፈንጠሪያዎች ላይ ይገኛሉ
    • በተመረጠው የአካባቢዎ ፀሐፊ ቢሮ ውስጥ በአካል በመቅረብ።

    የሞሉት ማመልከቻዎች ለእርስዎ በተመደበው ጽሕፈት ቤት በፖስታ፣ በኢሜይል ወይም በአካል በመቅረብ ከምርጫው ቀን በፊት ባለው ዓርብ ቀን ላይ እስከ 5:00 p.m. ድረስ መቅረብ አለበት።

    የእርስዎን የቀሪ ድምጽ መስጫ ወረቀትን መሙላት እና መመለስ

    የተሞላ ማመልከቻ ካስገቡ በኋላ የድምጽ መስጫ ወረቀት ወደ አድራሻዎ ይላካል። የእርስዎን የቀሪደምጽ መስጫ ወረቀት በአካል በመቅረብ በአከባቢዎ ወደ ተመደበልዎት የጽሕፈት ቤት ቢሮ የምርጫው ቀን በ 40 ቀናት ውስጥ በሚጎበኙበት ጊዜ ሊሰጥዎት ይችላል። 

    የእርስዎን የተሞላውን የቀሪ የድምጽ መስጫ ወረቀትን ለእርስዎ ወደተመደበው የቀሪ ድምጽ መስጫ ወረቀት ማስገቢያ ውስጥ ወይም ለከተማዎ፣ ለመንደሪዎ፣ ወይም የመንደሪዎ ጽሕፈት ቤት በምርጫው ቀን በ 8 p.m. ይመልሱ። በቀላሉ እንዲመልሱ ቀደም ተብሎ የተከፈለበት ፖስታ የሚሰጥዎት ሲሆን ለድምጽ መስጫ ወረቀቱ ምንም ዓይነት ወጪ አይኖርብዎትም።

    የተሞላው በአካል የማይገኝ መራጭ ድምጽ መስጫ ወረቀትን ለመመለስ ያሉ አማራጮች፡- 

    በኢንተርኔት ቀጥታ መስመር ላይ የ AV የደምጽ መስጫ ማመልከቻ 

    ሊታተም የሚችል የ AV ድምጽ መስጫ ማመልከቻ 

    የአካባቢዎን ፀሐፊ እና መቀበያ ቦታን ያግኙ  

  • በሚቺንጋን (Michigan) ቀደም ብሎ ድምጽ መስጠት

    በሚቺንጋን (Michigan) ድምጽ ሰጪዎች የድምጽ መስጫውን ቀደም ብለው ለማስገባት እና ከምርጫው ቀን በፊት ቀደም ብሎ ድምጽ መስጫ ቦታ ላይ በአካል ቀርበው ድምጽ ለመስጠት መብት አላቸው።  

    ቀደም ብሎ ድምጽ መስጠት በዋናነት ለፕሬዘዳንት በ 2024 ጀምሮ እና በእያንዳንዱ ግዛት እና በፌዴራል የምርጫ ከዚህ በኋላ የሚገኑ ይሆናል። 

    እንደ ሚቺንጋን (Michigan) ተመዝጋቢ ድምጽ ሰጪ፣ ቀደም ብለው ድምጽ ለመስጠት በሚመጡበት ቦታ ላይ የራስዎን አስተርጓሚ ይዘው የመመጣት መብት አልዎት። ማንኛውንም ሰው የእርስዎ አስተርጓም ሆኖ እንዲያገልግልዎት መጠየቅ ይችላሉ፤ ከሚከተሉት ግለሰቦች በስተቀር: 

    1. አሠሪዎ
    2. የአሠሪዎ ወኪል
    3. የሠራተኛ ማህበርዎ ባለስልጣን ወይም ወኪል

    ቀደም ብለው ድምጽ የሚሰጡት መቼ ነው

    ቀደም ብሎ ድምጽ መስጠት ጊዜ ቢያንስ ለተከታታይ ዘጠኝ ቀናት ያህል የሚቆይ ሲሆን፣ ከምርጫው በፊት እሁድ ላይ ያበቃል። ቀደም ብሎ ድምጽ ለመስጠት ተጨማሪ ቀናትን ለመመደብ፣ በአጠቃላይ እስከ 29 ቀናት ያህል ማኅበረሰቡ ሊወስን ይችላል።

    ቀደም ብለው ድምጽ የመስጫ ቦታዎች ቀደም ተብሎ ድምጽ በሚሰጥባቸው ጊዜያቶች ሁሉ በእያንዳንዱ ቀን ቢያንስ ለስምንት ሰዓታት ያህል ክፍት መሆን አለባቸው።

    ቀደም ብለው ድምጽ መስጠት ለግዛትም ሆነ ለፌዴራል ምርጫዎች ሁሉ የሚሰጡ ይሆናሉ። ማኅበረሰቦች ለአካባቢያዊ ምርጫዎች ቀደም ብሎ ድምጽ ስለመስጠት እንዲመደብ ምርጫ ሊያደርጉ ይችላሉ።

    ቀደም ብለው ድምጽ የሚሰጡባቸው ቦታዎች፣ ቀኖች፣ እና ሰዓታት ከምርጫው ቀናት ቀደም ብሎ ከ 60 ቀናት በፊት በ Michigan.gov/Vote ይገኛሉ።

    ቀደም ብሎ ድምጽ የሚሰጠው የት ነው

    ድምጽ ሰጪዎች በአከባቢያቸው የሚገኙትን ቀደም ብሎ የድምጽ መስጫ ቦታዎችን ቀደም ብሎ ድምጽ የመጫ ወቅት በአካል የድምጽ መስጫ ወረቀቱን ለማስገባት መጎብኘት ይችላሉ። ቀደም ብሎ ድምጽ መስጫ ቦታ መራጮች ከምርጫው ቀን ቀደም ብለው፣ ቀደም ብሎ ድምጽ መስጫ ተብሎ የተቀመጠው ወቅት የድምጽ መስጫ ወረቀታቸውን ለማስገባት የሚችሉበት የድምጽ መስጫ ሳጥን የሚመስል ነው። ከአንድ አከባቢ፣ ከተማ፣ ወይም መንደር ከመጡ ድምጽ ሰጪዎች በላይ የሚሆኑቱ በአንድ ቦታ ላይ፣ ቀደም ብሎ ድምጽ መስጫ ቦታዎን በመጋራት ድምጽ እንዲሰጥ ሊመደቡ ይችላሉ።

    ድምጽ ሰጪዎች ቀደም ብለው ድምጽ እንዲሰጡበት የተመደበላቸውን ቦያዎችን ከምርጫው ቀን በፊት ቀደም ብሎ እስከ 60 ቀናት ድረስ በ Michigan.gov/Voteላይ ሊመለከቱ ይችላሉ።

     

  • በራስ የመተርጎም ባህሪ ያለውን አሳሽ በመጠቀም የመራጮች የምዝገባ ሁኔታዎን በ Michigan.gov/Vote ላይ ማየት ይችላሉ።
    Browser translation – Language services

  • የድምጽ ሰጪን ማስፈራራት እና የምርጫ መከላከያ ነጻ መስመር

    ድምጽ ሰጪዎች ያለምንም ማስፈራራት ድምጻቸውን ለመስጠት መብት አላቸው። የድምጽ ሰጪዎችን ድምጽ የመስጠት መብት ውስጥ ጣልቃ መግባት ሕገወጥ ነው። የድምጽ ሰጪን ማስፈራሪያ በተመለከተ ሪፖርት ለማድረግ የምርጫ መከላከያ ነጻ መስመርን ይጠቀሙ።

    የድምጽ ሰጪን ማስፈራራት የሚያጠቃልላቸው፣ ነገር ግን በዚህ ብቻ የማይወሰን፡

    • የምርጫ ሠራተኞች ያልሆኑ ግለሰቦች ወይም የምርጫ ባለሥልጣናት ሆነው ድምጽ ሰጪዎችን የግል ሰነዳቸውን የሚጠይቁ
    • ያለ እነርሱ ፈቃድ የድምጽ ሰጪዎችን ���ቶ ማንሳት ወይም ቪዲዮ መቅረጽ
    • የድምጽ መስጫ ሳጥን ቦታዎችን፣ የጽሕፈት ቤት ቢሮን፣ ወይም የቀሪ ድምጽ መስጫ ወረቀት ማስገቢያ ቦታዎን መግቢያ መዝጋት
    • ድምጽ ሰጪዎችን በጥያቄ ማፋጠጥ ወይም ማዋረድ
    • ሐሰት የሆነ ወይም የሚያሳስተውን የምርጫመረጃን ማሰራጨት

    የድምጽ መስጫ ወረቀትዎን ሲያስገቡ ወይም ከምርጫው በፊት እነዚህ ነገሮች ቢያጋጥምዎት፣ ወይም የድምጽ መስጫ ሂደቱን በተመለከተ ጥያቄዎችን ካልዎት፣ የምርጫ መከላከያ ነጻ መስመርን በመጠቀም እገዛ ለማግኘት ያግኙን፦

    • ለእንግሊዝኛ፡ 866-OUR-VOTE (866-687-8683) 
    • ለስፓንሽ፦ 888-VE-Y-VOTA (888-839-8682) 
    • ለዓረብኛ፦ 844-YALLA-US (844-925-5287) 
    • ንጋሊ፣ ካንቶኒዝ ሂንዲ፣ ኮሪያኛ፣ ማንዳሪን፣ ታጋሎግ፣ ኡርዱ እና ቬትናምኛ፦ 888-API-VOTE (888-274-8683) 

    የቋንቋ አገልግሎት ማግኘት

    የሚቺንጋን (Michigan) ነዋሪዎች እንግሊዝኛ የአፍ መፍቻው ያልሆነን ተርጓሚ ወደ ጽሕፈት ቤት ቢሮ፣ ቀደም ተብሎ ድምጽ ለሚሰጥበት ቦታ ላይ ወይም ወደ ድምጽ መስጫ ሳጥን ድምጽ ለመስጠት ድጋፍ ለማግኘት ይዘው መምጣት መብት አላቸው። አስተርጓሚዎ በምርጫዎ ላይ ተጽዕኖ ሊያሳድር አይችልም፤ አሠሪዎ፣ የአሠሪዎ ወኪል ወይም የሠራተኛ ማህበርዎ ባለስልጣን ወይም ወኪል ሊሆን አይችልም።

    ምንም ዓይነት የሚታወቁበት ፎቶ አያስፈልግም

    የፎቶ መለያዎ ከእርስዎ ጋር ከሌለ፣ አሁንም ድምጽ መስጠት ይችላሉ።

    ምክንያት ሳይኖራቸው የቀሩ ድምጽ ሰጪዎች

    በሚቺንጋን (Michigan) ውስጥ ድምጽ ለመስጠት እያንዳንዱ ተመዝጋቢ የ የቀሪ ድምጽ መስጫን በመጠቀም ከቤት ድምጽ ለመስጠት፣ ቀደም ብሎ ድምጽ መስጠት፣ ወይም በፖስታ ድምጽ ለመስጠት መብት አላቸው።  በዚህ ማስፈንጠሪያ ላይ የበለጠ ይወቁ

    በተመሳሳይ ቀን ድምጽ ለመስጠት መመዝገብ

    ብቁ የሆኑ የሚቺጋን ከተማ ነዋሪዎች በምርጫ ቀን ድምጽ ለመስጠት የተመደበውን የአካባቢ ፀሐፊ ቢሮን በመጎብኘት እና የነዋሪነት ማረጋገጫን በማቅረብ መመዝገብ ይችላሉ። የነዋሪነት ማረጋገጫ የእርስዎን የአሁኑን ስም እና አድራሻ የያዘ ሕጋዊ ሰነዶች ማለት ሲሆን፣ የሚያጠቃልለውም (ነገር ግን በዚህ ብቻ የማይወሰን) የመንጃ ፈቃድ ወይም የግዛቱ መታወቂያ፣ የፍጆታ ደረሰኞ፣ የባንክ ወይም የክሬዲት ካርድ መግለጫ፣ ወይም የክፍያ ቼክን ያካትታል። የበለጠ በዚህ ላይ ይወቁ Michigan.gov/VoterRegistration

    ተመላሽ ዜጎች

    በሚቺንጋን (Michigan) ውስጥ፣ ተመላሽ ዜጎች፣ ወይም ያለፈው ጊዜ ጥፋት የነበራቸው ግለሰቦች፣ ምንም እንኳን በይቅርታ ወይም በክልከላ ላይ ያሉት እንኳን ቢሆኑ ለመመዝገብ ብቁ ናቸው። ከምርመራ በፊት ወይም ፍርዳቸውን እየጠበቁ ያሉ በእስር ላይ የሚገኝ ሰው ድምጽ ለመስጠት ለመመዝገብ እና ድምጽ ለመስጠት ቀሩ ለሆኑ ድምጽ መስጫ ወረቀትን በተመለከተ ለመመዝገብ ብቁ ናቸው።  በማረፊያ ቤት ውስጥ ወይም በእስር ላይ የሚገኙት ሰዎች ለመመዝገብ እና ድምጽ ለመስጠት የሚከለከልበት ብቸኛው ምክንያት እነዚህ ፍርድ ከተላለፈባቸው የሚገኙት ናቸው። የበለጠ በዚህ ላይ ይወቁ Michigan.gov/VoterRegistration

    የድምጽ ሰጪ ተደራሽነት

    የሚቺጋን ከተማ ድምጽ ሰጪዎች ተደራሽ የሆኑ የምርጫ ቦታዎችን የማግኘት እና የድምጽ አሰጣጥ እርዳታ ለማግኘት የመራጮች እርዳታ ተርሚናሎችን (Voter Assist Terminals፣ VATs) የመጠቀም መብት አላቸው። VAT ቶች የመስማት፣ የዕይታ፣ አካላዊ እክሎች እና ለሌሎች የአካል ጉዳቶች ላለባቸው ሰዎች፣ የምርጫ ካርዳቸው ላይ ምልክት ለማድረግ የሚረዱ የልዩ ሁኔታዎች መሳሪያዎች ናቸው። መራጮች VAT ን በመጠቀም በነፃነት እና በግል የመምረጥ መብት አላቸው እና በቦታው ላይ የምርጫ ተቆጣጣሪዎች (የድምጽ መስጫ ቦታ ሰራተኞች) ሲጠየቁ ለመርዳት ወይም መመሪያ ለመስጠት ዝግጁ ናቸው።

     
  • የሚከተሉት ማኅበረሰቦች በተወሰኑ ቋንቋዎች የተተረጎሙ የምርጫ ስነዶችን ያቀርባሉ።

    • የ(ዴኣብሪብ (Dearborn) ከተማ፦ ዓረብኛ
    • የሐመትራምክ (Hamtramck) ከተማ፦ ቤንጋሊ
    • የ ፌንቪሌ (Fennville) ከተማ፦ ስፓንሽ 
    • የ ኮልፌክስ ታዎንሽፕ (Colfax Township)፦ ስፓንሽ

    እንደ የተመዘገበ የሚቺጋን ከተማ ድምጽ ሰጪ፣ አስተርጓሚን ከእርስዎ ጋር ወደ ምርጫ ቦታው የማምጣት መብት አለዎት። ለበለጠ መረጃ ከላይ ያለውን "የድምጽ አሰጣጥ መብትዎ"ን ይመልከቱ። 

  • If you experience any issues casting your ballot on or before Election Day, contact the Election Protection Hotline for assistance:

    • ለእንግሊዝኛ ድጋፍ፣ ወደ 866-የእኛ-ምርጫ (866-687-8683) ይደውሉ
    • Para recibir ayuda en español, llama a 888-VE-Y-VOTA (888-839-8682)
    • ለአረብኛ ድጋፍ 844-YALLA-US (844-925-5287)
    • ለቤንጋሊኛ፣ ካንቶኒዝ፣ ህንድኛ፣ ኮርያኛ፣ ማንዳሪን፣ ታጋሎግኛ፣ ኡርዱ ወይም ቬትናምኛ ድጋፍ፣ ወደ 888-API-ምርጫ (888-274-8683) ይደውሉ
     

ቅጾች እና ህትመቶች

የቅጾች እና የህትመቶች ምናሌን በመጠቀም የተተረጎሙ የምርጫ መርጃዎችን እና ቁሳቁሶችን ይፈልጉ። ሁሉንም የተተረጎሙ ሰነዶችን እይ የሚለውን ለማጣራት Language ን ይጠቅሙ እና የፈለጉትን ቋንቋ ይምረጡ።

የተተረጎመ ሰነድ መጠየቅ

የተተረጎመውን ሰነድ ለመጠየቅ፣ እባክዎን በዚህ ላይ ኢሜይል ያድርጉ  MDOS-Access@Michigan.gov። እባክዎን የሚከተለውን መረጃ በኢሜይል መጠይቅዎ ውስጥ ያካትቱ፦

  • የሰነዱ ስም።
  • ለትርጉም የተጠየቀውን ቋንቋ